Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ዳግመኛም ሊጠገን እንደማይችል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሠራዊት አምላክ እንድነግራቸው ያዘዘኝም ቃል ይህ ነው፥ “ይህ የተሰበረ የሸክላ ገንቦ ተመልሶ ሊጠገን እንደማይችል፥ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ በዚሁ ዐይነት እሰባብራለሁ፤ ሰዎች ሙታናቸውን የሚቀብሩበት ሌላ ስፍራ ስለማይገኝ በቶፌት ይቀብሩአቸዋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ደግሞም ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፥ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 19:11
13 交叉引用  

በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥


አወ​ዳ​ደ​ቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደ​ቀቀ ይሆ​ናል፤ ሳይ​ራ​ራም ያደ​ቅ​ቀ​ዋል፤ ከስ​ባ​ሪ​ውም እሳት ከማ​ን​ደጃ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት፥ ወይም ውኃ ከጕ​ድ​ጓድ የሚ​ቀ​ዱ​በት ገል አይ​ገ​ኝም።”


ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”


እን​ዲሁ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ይህ​ች​ንም ከተማ እንደ ቶፌት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ር​ሳ​ታ​ለ​ሁም።


ስለ​ዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእ​ርድ ሸለቆ ይባ​ላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።


ሞአ​ብ​ንም ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም ዕቃ ሰብ​ሬ​አ​ለ​ሁና በሞ​አብ ሰገ​ነት ሁሉ ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህ​ንም መጽ​ሐፍ ማን​በብ ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ፥ ድን​ጋ​ይን እሰ​ር​በት፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ውስጥ ጣለው።


ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚ​መ​ስሉ የከ​በሩ የጽ​ዮን ልጆች፥ የሸ​ክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እን​ዴት ተቈ​ጠሩ!


ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።”


跟着我们:

广告


广告