Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነ​ርሱ ግን፥ “እን​ጨ​ክ​ና​ለን፤ ክዳ​ታ​ች​ንን ተከ​ት​ለን እን​ሄ​ዳ​ለን፥ ሁላ​ች​ንም ክፉ ልባ​ች​ንን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነርሱ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባቀድነው እንገፋበታለን፤ እያንዳንዳችንም የክፉ ልባችንን እልኸኝነት እንከተላለን’ ይላሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “እነርሱ ግን፦ ‘ተስፋ የለውም! አሳባችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም እንደ ክፉው ልባችን እልከኝነት እናደርጋለን’ አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነርሱም ‘ስለምን ብለን ይህን እናደርጋለን? እንዲያውም ያቀድነውን ሁሉ በመፈጸም ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞችና ዐመፀኞች መሆን እንችላለን’ ብለው ይመልሱልሃል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነርሱ ግን፦ እንጨክናለን፥ አሳባችንን ተከትለን እንሄዳለን ሁላችንም እንደ ክፉው ልባችን እልከኝነት እናደርጋለን አሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 18:12
18 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ገና እጠ​ብቅ ዘንድ ምን​ድን ነኝ?” አለ።


በመ​ን​ገ​ድ​ሽም ብዛት ደከ​ምሽ፤ ዳግ​መ​ኛም ጕል​በት እያ​ለኝ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ይህን መን​ገድ አል​ተ​ውም አላ​ል​ሽም፤ ይህ​ንም ስላ​ደ​ረ​ግሽ አላ​ፈ​ር​ሽም።


በጽ​ድቅ መን​ገድ ወደ​ማ​ይ​ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ወደ​ሚ​ከ​ተሉ ዐመ​ፀ​ኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆ​ችን ዘረ​ጋሁ።


እነ​ርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባ​ቸው እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ ስለ​ዚህ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱም ያላ​ደ​ረ​ጉ​ትን የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ አመ​ጣ​ሁ​ባ​ቸው።”


እና​ን​ተም ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ይልቅ ክፉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋል፤ እነ​ሆም ሁላ​ችሁ እንደ ክፉ ልባ​ችሁ ፍላ​ጎት ሄዳ​ች​ኋል፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


እግ​ር​ሽን ከሰ​ን​ከ​ል​ካላ መን​ገድ፥ ጕሮ​ሮ​ሽ​ንም ከውኃ ጥም ከል​ክዪ፤ እር​ስዋ ግን፥ “እጨ​ክ​ና​ለሁ፤ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ወድ​ጄ​አ​ለሁ” ብላ ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


ያን​ጊ​ዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ብለው ይጠ​ሩ​አ​ታል፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ክፉ​ውን እል​ከኛ ልባ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው አይ​ሄ​ዱም።


ነገር ግን እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን፥ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እና​ደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ ከአ​ፋ​ችን የወ​ጣ​ውን ቃል ሁሉ በር​ግጥ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ በዚያ ጊዜም እን​ጀ​ራን እን​ጠ​ግብ ነበር፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልን ነበር፤ ክፉም አና​ይም ነበር።


እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።


ነገር ግን በክፉ ልባ​ቸው አሳ​ብና እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ፤ ወደ​ፊ​ትም ሳይ​ሆን ወደ ኋላ​ቸው ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።


እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፣ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?


በክ​ንዱ ኀይ​ልን አደ​ረገ፤ በል​ባ​ቸው ዐሳብ የሚ​ታ​በ​ዩ​ት​ንም በተ​ና​ቸው።


“የዚ​ህ​ንም ርግ​ማን ቃሎች በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስን​ፍና በማ​ድ​ረግ ሄጃ​ለ​ሁና ይቅር ይለ​ኛል’ የሚል ቢኖር የበ​ደ​ለኛ ፍዳ ካል​በ​ደለ ጋር እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከል፥


跟着我们:

广告


广告