Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 17:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከቤ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ን​በት ቀን ሸክ​ምን አታ​ውጡ፤ ሥራ​ንም ሁሉ አት​ሥሩ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸው የሰ​ን​በ​ትን ቀን ቀድሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አባቶቻችሁን እንዳዘዝኋቸው ሰንበትን አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ከየቤታችሁ ሸክም ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከቤቶቻችሁም በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፥ ሥራንም ሁሉ አትሥሩበት፤ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁ የሰንበትን ቀን ቀድሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የቀድሞ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጋችሁ አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ ከቤታችሁ አትውጡ፤ በሰንበት ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከቤቶቻችሁም በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፥ ሥራንም ሁሉ አትሥሩበት፥ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁ የሰንበትን ቀን ቀድሱ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 17:22
19 交叉引用  

በዚ​ያም ወራት በይ​ሁዳ በሰ​ን​በት ቀን የወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያን የሚ​ረ​ግ​ጡ​ትን፥ ነዶም የሚ​ከ​ም​ሩ​ትን፥ የወ​ይ​ኑን ጠጅና የወ​ይ​ኑን ዘለላ፤ በለ​ሱ​ንም፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸክም በአ​ህ​ዮች ላይ የሚ​ጭ​ኑ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​ትን አየሁ፤ ገበ​ያም ባደ​ረ​ጉ​በት ቀን አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸው።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሁሉ ሥራ፤ በሬ​ህና አህ​ያህ ያርፉ ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህም ልጅ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም ዕረ​ፍት ይሆን ዘንድ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዕረፍ።


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


እኔን ፈጽሞ ብት​ሰሙ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን በዚ​ህች ከተማ በሮች ሸክም ባታ​ገቡ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን ብት​ቀ​ድሱ፥ ሥራ​ንም ሁሉ ባት​ሠ​ሩ​ባት፥


የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው።


ቅድ​ሳ​ቴ​ንም ናቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ።


ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይፍራ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፣ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፣ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ለሰ​ን​በት ጌታዋ ነው” አላ​ቸው።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


跟着我们:

广告


广告