Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አሳ​ዳ​ጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አል​ፈር፤ እነ​ርሱ ይደ​ን​ግጡ፤ እኔ ግን አል​ደ​ን​ግጥ፤ ክፉ​ንም ቀን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ በሁ​ለት እጥፍ ጥፋት ቀጥ​ቅ​ጣ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፤ እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ ክፉ ቀን አምጣባቸው፤ በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ሆይ! በሚያሳድዱኝ ሁሉ ላይ ኀፍረትን አምጣባቸው፤ እኔን ግን አታሳፍረኝ፤ እነርሱ እንዲሸበሩ አድርግ፤ እኔን ግን አታስደንግጠኝ፤ ተሰባብረው እስኪደቁ ድረስ ደጋግመህ አጥፋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፥ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፥ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 17:18
21 交叉引用  

በጦር ከበ​ቡኝ፤ ኵላ​ሊ​ቴ​ንም ወጉኝ፤ እነ​ር​ሱም አል​ራ​ሩ​ል​ኝም፤ ሐሞ​ቴ​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ።


በመ​ኝ​ታው ዐመ​ፅን ዐሰበ፤ በሁሉ ነገር መል​ካም ባል​ሆ​ነች መን​ገድ ቆሞ​አል፤ ክፋ​ት​ንም አይ​ሰ​ለ​ቻ​ትም።


ከቤ​ትህ ጠል ይረ​ካሉ። ከደ​ስ​ታ​ህም ፈሳሽ ታጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።


በጽ​ድ​ቅህ አስ​ጥ​ለኝ፥ ታደ​ገ​ኝም፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፥ ፈጥ​ነ​ህም አድ​ነኝ።


አቤቱ፥ ፍር​ድ​ህን ለን​ጉሥ ስጠው፥ ጽድ​ቅ​ህ​ንም ለን​ጉሥ ልጅ፥


አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኵላ​ሊ​ት​ንና ልብን የም​ት​ፈ​ትን፥ በቅ​ንም የም​ት​ፈ​ርድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ክር​ክ​ሬን ገል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና ከእ​ነ​ርሱ ፍረ​ድ​ልኝ።


አንተ ግን አቤቱ! ዐው​ቀ​ኸ​ኛል፤ አይ​ተ​ኸ​ኛል፤ ልቤ​ንም በፊ​ትህ ፈት​ነ​ሃል፤ እንደ በጎች ለመ​ታ​ረድ ጐት​ተህ ለያ​ቸው፤ ለመ​ታ​ረ​ድም ቀን አዘ​ጋ​ጃ​ቸው።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


ምድ​ሬ​ንም በተ​ጠሉ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሬሳ​ዎች አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ርስ​ቴ​ንም አስ​ጸ​ያፊ በሆኑ ነገ​ሮች ሞል​ተ​ዋ​ልና አስ​ቀ​ድሜ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንና የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።


እኔም አን​ተን ተከ​ትዬ አል​ደ​ከ​ም​ሁም፥ የሰ​ው​ንም ቀን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም፤ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ከከ​ን​ፈሬ የወ​ጣ​ውም በፊ​ትህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ሂድ፤ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በሚ​ገ​ቡ​በ​ትና በሚ​ወ​ጡ​በት በሕ​ዝ​ብህ ልጆች በር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች ሁሉ ቁም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለ​ዚህ አሳ​ዳ​ጆች ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ አያ​ሸ​ን​ፉም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የማ​ይ​ረሳ ጕስ​ቍ​ል​ና​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁ​ምና ፈጽ​መው አፈሩ።


አቤቱ ኀይ​ሉን ባርክ፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ ተቀ​በል፤ በሚ​ቃ​ወ​ሙት ጠላ​ቶቹ ላይ መከ​ራን አው​ርድ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ትም አይ​ነሡ።


እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


跟着我们:

广告


广告