Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አቤቱ! ፈው​ሰኝ፤ እኔም እፈ​ወ​ሳ​ለሁ፤ አድ​ነኝ፤ እኔም እድ​ና​ለሁ፤ አንተ መመ​ኪ​ያዬ ነህና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈውሰኝ፤ እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አቤቱ! ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር ሆይ፥ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ፤ ታደገኝ፤ እኔም በሰላም እኖራለሁ፤ ዘወትርም አንተን አመሰግናለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፥ አድነኝ እኔም እድናለሁ፥ አንተ ምስጋናዬ ነህና።

参见章节 复制




ኤርምያስ 17:14
23 交叉引用  

ጌታ ጌታ​ዬን፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለእ​ግ​ርህ መረ​ገጫ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” አለው።


የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ኝም እኔ ብና​ወጥ ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥


የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ኑ​ንም ሁሉ ምስ​ጋና ወደ እርሱ ለቀ​ረበ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም ቸል አት​በ​ለኝ።


ድውይ ነኝና አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አጥ​ን​ቶቼ ታው​ከ​ዋ​ልና ፈው​ሰኝ።


ነፍ​ሴም እጅግ ታወ​ከች፤ አን​ተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?


አቤቱ፥ ተመ​ለስ ነፍ​ሴ​ንም አድ​ናት፥ ስለ ቸር​ነ​ት​ህም አድ​ነኝ።


አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን ሰም​ተ​ሃ​ልና፤ ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።


እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው፥ ልባ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፍ​ነ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና።


ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።


በእ​ው​ነት የተ​ራ​ሮች ኀይል፥ የኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል መዳን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


እኔ ከክፉ ቍስ​ልሽ እፈ​ው​ስ​ሻ​ለሁ፤ ጤና​ሽን እመ​ል​ስ​ል​ሻ​ለሁ፤ ቍስ​ል​ሽ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ማንም የማ​ይ​ሻት፥ የተ​ጣ​ለች ጽዮን ብለው ጠር​ተ​ው​ሻ​ልና።”


“ኤፍ​ሬም ሲጨ​ነቅ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ ቀጣ​ኸኝ እኔም እን​ዳ​ል​ቀና ወይ​ፈን ተቀ​ጣሁ፤ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ነህና መል​ሰኝ፤ እኔም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


እነሆ ፈው​ስ​ንና መድ​ኀ​ኒ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እፈ​ው​ሳ​ታ​ለ​ሁም፤ የሰ​ላ​ም​ንና የእ​ው​ነ​ት​ንም መን​ገድ እገ​ል​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እየ​ጮኸ፥ “አቤቱ፥ እባ​ክህ፥ አድ​ናት” አለው።


ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፤ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ! አድነኝ፤” ብሎ ጮኸ።


ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! አድነን፤ ጠፋን፤” እያሉ አስነሡት።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​አ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ታላ​ላ​ቆች የከ​በ​ሩ​ትን ነገ​ሮች ያደ​ረ​ገ​ልህ እርሱ መመ​ኪ​ያ​ችሁ ነው፤ እር​ሱም አም​ላ​ክህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


跟着我们:

广告


广告