ኤርምያስ 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሰባት የወለደች ባዶ ቀረች፤ ነፍስዋም ተጨንቃለች፤ በቀትር ጊዜ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች፤ ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የሰባቶቹ እናት ትዝለፈለፋለች፤ ትንፋሿም ይጠፋል፤ ገና ቀን ሳለ ፀሓይዋ ትጠልቃለች፤ እርሷም ታፍራለች፤ ትዋረዳለችም፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት፣ ለሰይፍ እዳርጋቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፤ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች ተዋርዳለችም፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ይላል ጌታ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሰባት ልጆችዋን ያጣችው እናት፥ በታላቅ ተስፋ መቊረጥ ከእስትንፋስዋ ጋር እየታገለች ነው፤ የቀኑ ብርሃን ወደ ጨለማ ተለውጦባታል፤ ውርደትና ኀፍረት ደርሰውባታል፤ ገና በሕይወት ያላችሁትንም ጠላቶቻችሁ እንዲገድሉአችሁ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፥ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፥ አፍራለች ተዋርዳማለች፥ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ። 参见章节 |