ኤርምያስ 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አንቺ እኔን ከድተሽኛል፤ እኔንም መከተል ትተሻል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ፤ ይቅርም አልላቸውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እኔን ጥለሽኛል” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ ኋላም እያፈገፈግሽ ነው፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ አጠፋሻለሁም፤ ከእንግዲህም አልራራልሽም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አንቺ እኔን ትተሺኛል፥ ይላል ጌታ፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ይቅርታን ከማድረግ ደክሜአለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እናንተ እኮ እኔን ትታችሁኛል፤ እናንተ ወደ ኋላ ተመልሳችኋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ምሕረት አላደርግም፤ እጄን ዘርግቼ አደቃችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አንቺ እኔን ጥለሻል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፥ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፥ ከይቅርታ ደክሜአለሁ። 参见章节 |