Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ “ ‘ድንግሊቱ ልጄ፣ ሕዝቤ፣ በታላቅ ስብራት፣ በብርቱ ቍስል ተመትታለችና ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት፣ ሳያቋርጡ እንባ ያፈስሳሉ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና ፈጽሞ በማይሽር ቁስል ቆስላለችና ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ። “ሕዝቤ እጅግ ቈስሎአል፤ በብርቱም ተጐድቶአል፤ ስለዚህ ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት እንባ ያፈሳሉ፤ ባለማቋረጥም አለቅሳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 14:17
20 交叉引用  

ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ፥ ሰድ​ቦ​ሻ​ልና ንቆ​ሻ​ል​ምና፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ፥ በአ​ንቺ ላይ ራሱን ነቅ​ን​ቋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦


ቅን​ነ​ት​ህን በልቤ ውስጥ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም፥ ማዳ​ን​ህ​ንም ተና​ገ​ርሁ፤ ይቅ​ር​ታ​ህ​ንና ምሕ​ረ​ት​ህን ከታ​ላቅ ጉባኤ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፦ ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ቀላል አድ​ር​ጋ​ሃ​ለች፤ በን​ቀ​ትም ሥቃ​ብ​ሃ​ለች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጅ ራስ​ዋን ነቅ​ን​ቃ​ብ​ሃ​ለች።


ስለ ስብ​ራቴ ወዮ​ልኝ! ቍስ​ሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእ​ው​ነት የመ​ከራ ቁስሌ ነው፤ እር​ሱ​ንም መሸ​ከም ይገ​ባ​ኛል አልሁ።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን በጣም የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን ነገር የሚ​ሰ​ሙት እን​ዳለ አሕ​ዛ​ብን ጠይቁ።”


ልባ​ች​ሁን ታም​ማ​ችሁ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዛ​ላ​ችሁ። ከሚ​ያ​ቅ​በ​ዘ​ብዝ የልብ ሕመ​ማ​ችሁ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ የለም።


በሕ​ዝቤ ሴት ልጅ ስብ​ራት እኔ ወድቄ ተሰ​ብ​ሬ​አ​ለሁ፤ ጠቍ​ሬ​ማ​ለሁ፤ ራስ ማዞ​ርም ይዞ​ኛል፤ ምጥ እን​ደ​ያ​ዛ​ትም ሴት በመ​ከ​ራው እጨ​ነ​ቃ​ለሁ።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


ፈጥ​ነ​ውም ሙሾ ያሙ​ሹ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም እን​ባን ያፍ​ስሱ፤ ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ሽፋ​ሽ​ፍ​ቶች ውኃ ይፍ​ለቅ።


ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ።


ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?


ጻዴ። ልባ​ቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እን​ባ​ሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍ​ስሺ፤ ለሰ​ው​ነ​ትሽ ዕረ​ፍት አት​ስጪ፤ የዐ​ይ​ን​ሽ​ንም ብሌን አታ​ቋ​ርጪ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፥ ስለ ኃጢአትህም አፈረስሁህ።


跟着我们:

广告


广告