Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ከራ​ብና ከሰ​ይፍ የተ​ነሣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ይበ​ተ​ናሉ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እነ​ር​ሱ​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው አይ​ገ​ኝም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ትንቢቱ የተነገረለትም ሕዝብ ከሰይፍና ከራብ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይወድቃል፤ እነርሱንም ሆነ ሚስቶቻቸውን ወይም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይገኝም። ለበደላቸው የሚገባውንም ቅጣት በላያቸው አወርዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይጣላሉ፤እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም፤ ክፋታቸውንም በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህንንም የተነበዩላቸው ሕዝብ ሁሉ በራብና በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውም ሁሉ በኢየሩሳሌም ውስጥ በየመንገዱ ይወድቃል፤ የሚቀብራቸውም አይኖርም፤ ይህም በሚስቶቻቸው፥ በወንዶች ልጆቻቸውና በሴቶች ልጆቻቸው ሳይቀር በሁሉም ላይ ይፈጸማል፤ በበደላቸውም መጠን ተገቢ ቅጣታቸውን እሰጣቸዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፥ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 14:16
23 交叉引用  

ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።


ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።


ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤


“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


አን​ተም ጳስ​ኮር ሆይ! በቤ​ት​ህም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ተማ​ር​ካ​ችሁ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ አን​ተም በሐ​ሰት ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ በዚ​ያም ትቀ​በ​ራ​ላ​ችሁ።”


እኔ አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን እኔ እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተና ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ነቢ​ያ​ትም እን​ድ​ት​ጠፉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


መን​ገ​ድ​ሽና ክፉ ሥራሽ ይህን አድ​ር​ጎ​ብ​ሻል፤ ይህ ክፋ​ትሽ መራራ ነው፤ ወደ ልብ​ሽም ደር​ሶ​አል።


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


የዚህ ሕዝብ ሬሳ ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው የለ​ምና።


“በዚ​ያም ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትን አጥ​ን​ትና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን አጥ​ንት፥ የካ​ህ​ና​ቱን አጥ​ን​ትና የነ​ቢ​ያ​ቱን አጥ​ንት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሰዎች አጥ​ንት ከመ​ቃ​ብ​ሮ​ቻ​ቸው ያወ​ጣሉ።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


እና​ንተ ሴቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጆሮ​አ​ች​ሁም የአ​ፉን ቃል ትቀ​በል፤ ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ልቅ​ሶ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድ​ዋም ለባ​ል​ን​ጀ​ራዋ ዋይ​ታን ታስ​ተ​ምር።


የሰ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእ​ርሻ ላይ፥ ማንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​በ​ስ​በው ከአ​ጫ​ጆች በኋላ እን​ደ​ሚ​ቀር ቃር​ሚያ ይወ​ድ​ቃል።


ምድ​ር​ንም ለማ​ጽ​ዳት በም​ድሩ ላይ ወድ​ቀው የቀ​ሩ​ትን የሚ​ቀ​ብሩ፥ ዘወ​ትር በም​ድሩ ላይ የሚ​ዞ​ሩ​ትን ሰዎች ይቀ​ጥ​ራሉ፤ ከሰ​ባት ወርም በኋላ ይመ​ረ​ም​ራሉ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሚስ​ትህ በከ​ተ​ማ​ይቱ ውስጥ አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ር​ህም በገ​መድ ትከ​ፈ​ላ​ለች፤ አን​ተም በረ​ከ​ሰች ምድር ትሞ​ታ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከም​ድሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል።”


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告