ኤርምያስ 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፥ “መቅበዝበዝን ወድደዋል፤ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፤ በደላቸውንም አሁን ያስባል፤ ኀጢአታቸውንም ይጐበኛል።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እግዚአብሔር ስለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፤ “መቅበዝበዝ እጅግ ይወድዳሉ፤ እግሮቻቸው አይገቱም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፤ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ጌታ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “በእውነት መቅበዝበዝን ወድደዋል፥ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ ጌታ በእነርሱ ደስ አይሰኝም፥ በደላቸውንም አሁን ያስታውሳል ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ከእኔ ርቀው መሄድ ይወዳሉ፤ ራሳቸውንም አይቈጣጠሩም፤ ስለዚህ እኔ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ የፈጸሙትን በደል ሁሉ በማስታወስ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ መቅበዝበዝን ወድደዋል እግራቸውንም አልከለከሉም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፥ በደላቸውንም አሁን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል። 参见章节 |