Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከነ​ቀ​ል​ኋ​ቸ​ውም በኋላ መልሼ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ሁላ​ቸ​ው​ንም በር​ስ​ታ​ቸው፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ው​ንም በም​ድ​ራ​ቸው አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከነቀልኋቸው በኋላ ግን መልሼ እምራቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውንም ወደ ገዛ አገራቸውና ወደ ገዛ ርስታቸው መልሼ አመጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን ከአገራቸው ካወጣኋቸው በኋላ እንደገና ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሕዝብ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ አገሩ መልሼ አመጣዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 12:15
16 交叉引用  

ነገር ግን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሰ​ሜን ምድር፥ ከተ​ሰ​ደ​ዱ​በ​ትም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይባ​ላል፤ እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ኋት ወደ ምድ​ራ​ቸው እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ዐይ​ኔ​ንም ለበ​ጎ​ነት በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ምድር ለመ​ል​ካም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ቸ​ውም፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ቸ​ውም።


እገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምር​ኮ​አ​ች​ሁ​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ እና​ን​ተ​ንም ከበ​ተ​ን​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እና​ን​ተ​ንም ለም​ርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ስ​ሁ​በት ስፍራ እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።


ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመ​ለሽ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አል​ቈ​ጣ​ምና በእ​ና​ንተ ላይ ፊቴን አላ​ጸ​ናም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ያን​ጊ​ዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ብለው ይጠ​ሩ​አ​ታል፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ክፉ​ውን እል​ከኛ ልባ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው አይ​ሄ​ዱም።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


ነገር ግን በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሞ​አ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የሞ​ዓብ ፍርድ እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።


ነገር ግን በኋ​ለ​ኛው ዘመን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የኤ​ላ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአ​ሞ​ንን ልጆች ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች ሠር​ተው ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ን​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ የወ​ይን ጠጃ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ተክ​ልን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤


ከዚ​ህም በኋላ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት መልሼ እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤ ፍራ​ሽ​ዋ​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤


ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ት​ህን ይቅር ይል​ሃል ይራ​ራ​ል​ህ​ማል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ከበ​ተ​ነ​በት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መልሶ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል።


跟着我们:

广告


广告