Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ል​ሁ​ትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፥ “አቤቱ! ጌታ ሆይ! ይሁን” ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የገባሁትን መሐላ እፈጽማለሁ።’ ” እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ አሜን” ብዬ መለስሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፦ አቤቱ፥ አሜን ብዬ መለስሁለት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 11:5
16 交叉引用  

አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ይጽና።


ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ና​ንተ ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ​ማ​ለ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር፥ ወደ ከና​ኔ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጢ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ምድር በአ​ገ​ባ​ችሁ ጊዜ ይህ​ችን ሥር​ዐት በዚህ ወር አድ​ርጉ።


እን​ዲሁ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ይህ​ች​ንም ከተማ እንደ ቶፌት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ር​ሳ​ታ​ለ​ሁም።


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ፥ ምር​ኮ​ው​ንም ሁሉ ከባ​ቢ​ሎን ወደ​ዚህ ስፍራ በመ​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ትን​ቢት ይፈ​ጽም።


ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ህ​ላ​ቸ​ውን ምድር፥ ወተ​ትና ማርም የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ሰጠ​ሃ​ቸው፤


ነገር ግን እና​ንተ፦ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ አል​ኋ​ችሁ፤ እኔ ከአ​ሕ​ዛብ የለ​የ​ኋ​ችሁ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


አንተ በመ​ን​ፈስ ብታ​መ​ሰ​ግን፥ ያ የቆ​መው ያል​ተ​ማ​ረው በአ​ንተ ምስ​ጋና ላይ እን​ዴት አሜን ይላል? የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና የም​ት​ጸ​ል​የ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና።


እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጥህ ዘንድ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ እጅግ እን​ድ​ት​በዛ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በም​ድረ በዳ ያዘ​ዛ​ቸው ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው።


跟着我们:

广告


广告