ኤርምያስ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበችና የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመቈረጥዋም ድምፅ የተነሣ በላይዋ እሳት ነደደባት፤ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እግዚአብሔር፣ የተዋበ ፍሬ ያላት፣ የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎሽ ነበር፤ አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣ እሳት ያነድድባታል፤ ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፥ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። 参见章节 |