Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 11:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያን ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ መሥዋዕት ወደሚያቀርቡላቸው ባዕዳን አማልክት ሄደው ርዳታ እንዲያደርጉላቸው ይጮኻሉ፤ ነገር ግን እነርሱ ይህ ጥፋት በሚመጣበት ጊዜ ሊያድኑአቸው አይችሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 11:12
10 交叉引用  

ዳግ​መ​ኛም ንጉሡ አካዝ ፈጽሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቀ።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።


ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።


ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ታጠፉ ዘንድ፥ በም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መረ​ገ​ሚ​ያና መሰ​ደ​ቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመ​ቀ​መጥ በገ​ባ​ች​ሁ​ባት በግ​ብፅ ምድር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት በማ​ጠ​ና​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ለምን ታስ​ቈ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ ትታ​መ​ኑ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩት አማ​ል​ክት የት አሉ?


የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ስብ የም​ት​በ​ሉ​ላ​ቸው፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ች​ው​ንም ወይን የም​ት​ጠ​ጡ​ላ​ቸው፥ እነ​ርሱ ይነሡ፤ ይር​ዱ​አ​ች​ሁም፤ የሚ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።”


跟着我们:

广告


广告