ኤርምያስ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፥ “ምን ታያለህ?” እኔም፥ “የሚፈላ አፍላል አያለሁ፤ ፊቱም ወደ ሰሜን ወገን ነው” አልሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም፣ “አንድ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደዚህ ያዘነበለ ነው” አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሁለተኛም ጊዜ የጌታ ቃል “ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም “የሚፈላ የሸክላ ድስት ከሰሜን ፊቱን አዘንብሎ አያለሁ” አልሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እንደገናም እግዚአብሔር “ሌላስ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “በስተ ሰሜን በኩል አንድ ማሰሮ ሲፈላ አያለሁ፤ ወደዚህም ለመገልበጥ አዘንብሎአል” ስል መለስኩለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፦ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፦ የሚፈላ አፍላል አያለሁ፥ ፊቱም ከሰሜን ወገን ነው አልሁ። 参见章节 |