Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ያዕቆብ 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከእናንተ መካከል በመከራ ውስጥ ያለ አለ? እርሱ ይጸልይ፤ የተደሰተ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከእናንተ መካከል ችግር የደረሰበት ሰው ቢኖር ይጸልይ፤ ደስ ያለው ሰውም ቢኖር እግዚአብሔርን በማመስገን ይዘምር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።

参见章节 复制




ያዕቆብ 5:13
34 交叉引用  

ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ኙ​ለት፥ ዘም​ሩ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ሁሉ ተና​ገሩ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ያል፥ ጸሎ​ቱም ተቀ​ባ​ይ​ነ​ትን ያገ​ኛል። በደ​ስ​ተ​ኛም ፊት እያ​መ​ሰ​ገነ ይገ​ባል፥ ለሰ​ውም ጽድ​ቁን ይመ​ል​ስ​ለ​ታል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል? ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል?


ሥር​ዐ​ት​ህን እጠ​ብቅ ዘንድ የሚ​ቀ​ናስ ከሆነ መን​ገዴ ይቅና።


አወ​ጣጡ ከሰ​ማ​ያት ዳርቻ ነው፥ መግ​ቢ​ያ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከት​ኩ​ሳ​ቱም የሚ​ሰ​ወር የለም።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለ​ትም ማዳ​ኑን አውሩ።


እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ፤ እና​ንተ ግን ከል​ባ​ችሁ ኀዘን የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ስለ ተሰ​በረ ወዮ! ትላ​ላ​ችሁ።


በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።


ዮና​ስም በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።


ሕዝብም ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል፥ እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም እንሄዳለን።


መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።


ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።


እን​ግ​ዲህ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ በመ​ን​ፈስ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈሴ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እዘ​ም​ራ​ለሁ።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ሁላ​ችሁ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ መዝ​ሙር አላ​ችሁ፤ ትም​ህ​ርት አላ​ችሁ፤ መግ​ለጥ አላ​ችሁ፤ በቋ​ንቋ መና​ገር አላ​ችሁ፤ መተ​ር​ጐ​ምም አላ​ችሁ፤ ሁሉም ለሚ​ታ​ነ​ጽ​በት ጥቅም አድ​ር​ጉት።


መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የተ​ቀ​ደሰ ማሕ​ሌ​ት​ንም አን​ብቡ፤ በል​ባ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀኙ፤ ዘም​ሩም።


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


ወንድሞች ሆይ! የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ።


በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።


በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።


跟着我们:

广告


广告