Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ብዙ ሕዝ​ብን በደ​ስታ አወ​ረ​ድህ፤ በመ​ከር ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው፥ ምር​ኮ​ንም እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ በፊ​ትህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አበዛህ፤ በደስታም እንዲሞሉ አደረግሃቸው፤ ሰዎች መከር በሚሰበስቡበት፥ ወይም ምርኮ በሚካፈሉበት ጊዜ ደስ እንደሚላቸው ሕዝብህም አንተ ባደረግኸው ነገር ደስ ይላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፥ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 9:3
38 交叉引用  

ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው።


አሕ​ዛ​ብን ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ልም፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ልም።


በል​ባ​ችን ደስ​ታን ጨመ​ርህ፤ ከስ​ንዴ ፍሬና ከወ​ይን፥ ከዘ​ይ​ትም ይልቅ በዛ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ያ​ምን በመ​ከ​ራው ቦታ እንደ መታው ጅራ​ፍን ያነ​ሣ​በ​ታል፤ ቍጣ​ውም በባ​ሕሩ መን​ገ​ድና በግ​ብፅ መን​ገድ በኩል ይሆ​ናል።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን ቀን​በ​ርና የአ​ለ​ቆ​ችን ቀን​በር ሰብ​ሮ​አ​ልና።


በዚ​ያም ቀን፥ “እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድ​ር​ገ​ነ​ዋል፤ ያድ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ ነው፤ ጠብ​ቀ​ነ​ዋል፤ በመ​ዳ​ና​ች​ንም ደስ ይለ​ናል፤ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን” ይላሉ።


አቤቱ፥ ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፤ ለም​ድር ክቡ​ራን ክፋ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ምድረ በዳ ያብ​ባል፤ ሐሤ​ት​ንም ያደ​ር​ጋል፤ የሊ​ባ​ኖስ ክብ​ርና የቀ​ር​ሜ​ሎስ ክብር ይሰ​ጠ​ዋል፤ ሕዝ​ቤም የጌ​ታን ክብር፥ የአ​ም​ላ​ክ​ንም ግርማ ያያሉ።


አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እና​ን​ተም በደ​ስታ ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ በሐ​ሤ​ትም ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በደ​ስታ ሊቀ​በ​ሏ​ችሁ ይዘ​ላሉ፤ የሜ​ዳም ዛፎች ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቻ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።


ሌላ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ደስታ አላ​ቸው።


እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ፤ እና​ንተ ግን ከል​ባ​ችሁ ኀዘን የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ስለ ተሰ​በረ ወዮ! ትላ​ላ​ችሁ።


ነገር ግን በው​ስ​ጥዋ ደስ​ታ​ንና ሐሤ​ትን ያገ​ኛሉ፤ እኔም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደስ​ታን ለሕ​ዝ​ቤም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ ደስ ይበ​ልሽ፤ እር​ስ​ዋ​ንም የም​ት​ወ​ድ​ዱ​አት ሁሉ፥ በአ​ን​ድ​ነት ሐሤት አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ስ​ዋም ያለ​ቀ​ሳ​ችሁ ሁሉ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ አድ​ኖ​አል በሉ።


እንደ ብዛ​ታ​ቸው መጠን ኀጢ​አት ሠሩ​ብኝ፤ እኔም ክብ​ራ​ቸ​ውን ወደ ውር​ደት እለ​ው​ጣ​ለሁ።


ባሪ​ያ​ዎች ከነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ የባ​ር​ነ​ታ​ች​ሁን ቀን​በር ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፤ በግ​ል​ጽም አወ​ጣ​ኋ​ችሁ።


ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፣ ቀድሞም በዝተው እንደ ነበሩ ይበዛሉ።


በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።


ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል።


በዚ​ያ​ችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።


ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።


ነገ​ሥ​ታት ሆይ፥ ስሙ፤ ጽኑ​ዓን መኳ​ን​ን​ትም ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ እኔ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እቀ​ኛ​ለሁ፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ም​ራ​ለሁ።


ሦስ​ቱ​ንም መቶ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ውን ሁሉ ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ዉና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ አደ​ረገ፤ ሠራ​ዊ​ቱም በጽ​ሬራ በኩል እስከ ቤት​ሲጣ ጋራ​ጋታ ድረስ በጣ​ባት አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው እስከ አቤ​ል​ሜ​ሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ።


ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ሸሹ፤ እር​ሱም አሳ​ደ​ዳ​ቸው፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ያዘ፤ ጌዴ​ዎ​ንም ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ አጠፋ።


ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告