Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኀጢ​አት እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ እሳት እንደ በላ​ችው ደረቅ ሣር ይቃ​ጠ​ላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃ​ጠ​ላል፤ በተ​ራ​ራ​ዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃ​ጠ​ላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሠራዊት ጌታ ቁጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፥ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፥ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 9:18
36 交叉引用  

በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ በሁ​ለት ተከ​ፈለ፤ የሕ​ዝ​ቡም እኩ​ሌታ የጎ​ና​ትን ልጅ ታም​ኒን ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ተከ​ተ​ሉት፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም ዘን​በ​ሪን ተከ​ተሉ።


በበጎ ፋንታ ክፉን የሚ​መ​ል​ሱ​ልኝ ጽድ​ቅን ስለ ተከ​ተ​ልሁ ይከ​ስ​ሱ​ኛል። እንደ ርኩስ በድን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን ጣሉ፥


በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።


ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራ​ቸ​ውም እንደ ጠለ​ሸት ይሆ​ናል፤ ኃጥ​አ​ንና ዐማ​ፅ​ያ​ንም አብ​ረው ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እሳ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው ያጣሉ።”


ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።


ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል።


ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”


በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው?


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


እነሆ፥ እሳት የም​ታ​ነ​ድዱ፥ የእ​ሳ​ት​ንም ነበ​ል​ባል ከፍ ያደ​ረ​ጋ​ችሁ ሁላ​ችሁ፥ በእ​ሳ​ታ​ችሁ ብር​ሃ​ንና ባነ​ደ​ዳ​ች​ሁት ነበ​ል​ባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል፤ በኀ​ዘ​ንም ትተ​ኛ​ላ​ችሁ።


“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።


የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”


እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ግ​ሮ​አ​ልና የያ​ዕ​ቆብ ቤት እሳት፥ የዮ​ሴ​ፍም ቤት ነበ​ል​ባል፥ የዔ​ሳ​ውም ቤት ገለባ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ው​ማል፤ ከዔ​ሳ​ውም ቤት ቅሬታ አይ​ኖ​ርም።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።


እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ትን ብታ​ወጣ ግን የተ​ጣ​ለች ናት፤ ለመ​ር​ገ​ምም የቀ​ረ​በች ናት፤ ፍጻ​ሜ​ዋም ለመ​ቃ​ጠል ይሆ​ናል።


የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”


跟着我们:

广告


广告