Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወደ ታችም ወደ ምድር ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማ​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ታላቅ መከ​ራ​ንም ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትቸ​ገ​ራ​ላ​ች​ሁም፤ በፊ​ታ​ች​ሁም ጨለማ ይሆ​ናል፤ አታ​ዩ​ምም፤ በመ​ከ​ራም ያለ ጊዜው እስ​ኪ​ደ​ርስ አይ​ድ​ንም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፤ የሚያዩትም ጭንቀት፤ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ሲመለከቱ ሊያዩ የሚችሉት ጭንቀት ጨለማና ጭፍግግ ያለ አስፈሪ ሁኔታን ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ወደ ምድርም ይመለከታሉ፥ እነሆም፥ መከራና ጨለማ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ፥ ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 8:22
25 交叉引用  

ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ አር​ቀው ያፈ​ል​ሱ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለ​ማ​ውም የሚ​ዳ​ሰስ ነው” አለው።


ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለ​ማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤


ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።


እነሆ፥ እሳት የም​ታ​ነ​ድዱ፥ የእ​ሳ​ት​ንም ነበ​ል​ባል ከፍ ያደ​ረ​ጋ​ችሁ ሁላ​ችሁ፥ በእ​ሳ​ታ​ችሁ ብር​ሃ​ንና ባነ​ደ​ዳ​ች​ሁት ነበ​ል​ባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል፤ በኀ​ዘ​ንም ትተ​ኛ​ላ​ችሁ።


ሰማ​ይን በጨ​ለማ እሸ​ፍ​ነ​ዋ​ለሁ፤ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ማቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ።”


ስለ​ዚህ ፍርድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርቆ​አል፤ ጽድ​ቅም አላ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ ብር​ሃ​ንን ሲጠ​ባ​በቁ ብር​ሃ​ና​ቸው ጨለማ ሆነ​ባ​ቸው፤ ብር​ሃ​ን​ንም ሲጠ​ባ​በቁ በጨ​ለማ ሄዱ፤


እነሆ፥ ጨለማ ምድ​ርን፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም አሕ​ዛ​ብን ይሸ​ፍ​ናል፤ ነገር ግን በአ​ንቺ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጣል፤ ክብ​ሩም በአ​ንቺ ላይ ይታ​ያል፤


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


የዚ​ህም ጊዜው እስ​ከ​ሚ​ደ​ርስ የተ​ቸ​ገ​ረው ሁሉ አያ​መ​ል​ጥም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዘመን የዛ​ብ​ሎ​ን​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምን ምድር አቃ​ለለ፤ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ግን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር መን​ገድ ያለ​ውን የአ​ሕ​ዛ​ብን ገሊላ ያከ​ብ​ራል።


ነገር ግን ሰው ወደ ቀኙ ይመ​ለ​ሳል፤ ይራ​ባ​ልና፤ በግ​ራም በኩል ይበ​ላል፤ አይ​ጠ​ግ​ብ​ምም፤


ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚህ መን​ገ​ዳ​ቸው ድጥና ጨለማ ትሆ​ን​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ፍግ​ም​ግም ብለው ይወ​ድ​ቁ​ባ​ታል፤ እኔም በም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ዓመት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤


跟着我们:

广告


广告