Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የአ​ራም ራስ ደማ​ስቆ ነው፤ የደ​ማ​ስ​ቆም ራስ ረአ​ሶን ነው፤ በስ​ድሳ አም​ስት ዓመት ውስጥ የኤ​ፍ​ሬም መን​ግ​ሥት ከሕ​ዝብ ይጠ​ፋል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፣ የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤ በስድሳ ዐምስት ዓመት ውስጥ፣ የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብ መሆኑም ይቀራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፤ የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤ በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፤ የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብ መሆኑም ይቀራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለምን ቢባል፥ የሶርያ ራስ ደማስቆ ስትሆን፥ የደማስቆም ራስ ረጺን ነው፤ ስለ እስራኤልም የሆነ እንደ ሆነ፥ በስልሳ አምስት ዓመቶች ጊዜ ውስጥ ብትንትናቸው ወጥቶ በመንግሥትነት መታወቃቸው ይቀራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሶርያ ራስ ደማስቆ ነው፥ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፥ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 7:8
12 交叉引用  

እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ወደ ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ወደ አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “የአ​ሦር ንጉሥ አስ​ራ​ዶን ወደ​ዚህ ካመ​ጣን ቀን ጀምሮ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና፥ እንደ እና​ን​ተም እን​ፈ​ል​ገ​ዋ​ለ​ንና ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሥራ” አሉ​አ​ቸው።


ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


የኤ​ፍ​ሬም ሕዝብ ሁሉና በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖሩ ያው​ቃሉ፤ በት​ዕ​ቢ​ትና በልብ ኵራ​ትም እን​ዲህ ይላሉ፦


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


ከሥ​ራሽ ብዛ​ትና ከብ​ል​ጽ​ግ​ናሽ ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የደ​ማ​ስቆ ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ በኬ​ል​ቦን የወ​ይን ጠጅ፥ በነ​ጭም የበግ ጠጕር ይነ​ግዱ ነበር።


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


跟着我们:

广告


广告