Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በሚ​ታ​ረ​ሰ​ውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ የበ​ጎች መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ናል፤ በሬ​ዎ​ችም ይረ​ግ​ጡ​ታል፤ እሾ​ህና ኵር​ን​ች​ትም ያጠ​ፋ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኵርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደ ነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብቶች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኩርርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብታዎች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ቀድሞ በዶማ ተቈፍረው እህል ይበቅልባቸው የነበሩ ኰረብቶች ሁሉ ኲርንችትንና እሾኽን በመፍራት ማንም ወደዚያ አይሄድም፤ ነገር ግን የከብትና የበግ መንጋ መሰማሪያ ብቻ ይሆናሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተንሣ ወደዚያ አትሄድም፥ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 7:25
8 交叉引用  

ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ለመ​ንጋ ማሰ​ማ​ር​ያም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም የለም።


የተ​ማ​ረኩ እንደ በሬ​ዎች ይሰ​ማ​ራሉ፤ የተ​ረ​ሱ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሲፈ​ልጉ እንደ በግ ጠቦ​ቶች በማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ይሰ​ማ​ራሉ።


ይመ​ጡ​ማል፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሸ​ለቆ፥ በመ​ን​ደ​ሮች፥ በም​ድር ጕድ​ጓድ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰ​ፍ​ራሉ።


በፍ​ላ​ጻና በቀ​ስት ይገ​ቡ​ባ​ታል፤ ምድ​ሪቱ ሁሉ ትጠ​ፋ​ለ​ችና፥ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለ​ችና።


እስ​ራ​ኤል እን​ደ​ም​ት​ደ​ነ​ብር ጊደር ደን​ብ​ሮ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰ​ማ​ራ​ዋል።


ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告