Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ወይን በሀ​ገሩ ሁሉ የበጀ ይሆ​ናል፤ የአ​ንድ ሺህ የወ​ይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆ​ናል። ከዚህ በኋላ ዳግ​መኛ ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለች፤ ፍር​ሀ​ትም ይመ​ጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚያ ቀን ሺሕ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺሕ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በዚያን ቀን ሺህ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺህ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፤ ኩርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “በዚያም ቀን ግምቱ ሺህ ብር የሚሆን አንድ ሺህ ምርጥ የወይን ተክል እንዲለማ የተደረገበት ቦታ ሁሉ ኲርንችትና እሾኽ ይበቅልበታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ሥፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ይሆናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 7:23
13 交叉引用  

እሾ​ህ​ንና አሜ​ከ​ላን ታበ​ቅ​ል​ብ​ሃ​ለች፤ የም​ድ​ር​ንም ቡቃያ ትበ​ላ​ለህ።


በየ​ዓ​መቱ የኀ​ዘን በዓል መታ​ሰ​ቢያ አድ​ርጉ፤ ወይን መቍ​ረጥ አል​ፎ​አል፤ ፍሬ ማከ​ማ​ች​ትም አል​ቆ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​መ​ጣም።


ዐሥር ጥማድ በሬ ካረ​ሰው የወ​ይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወ​ጣል፤ ስድ​ስት መስ​ፈ​ሪያ የዘራ ሦስት መሥ​ፈ​ሪያ ብቻ ያገ​ባል።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


በፍ​ላ​ጻና በቀ​ስት ይገ​ቡ​ባ​ታል፤ ምድ​ሪቱ ሁሉ ትጠ​ፋ​ለ​ችና፥ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለ​ችና።


ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ቀር​ሜ​ሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተ​ሞ​ችም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣ​ውም የተ​ነሣ ፈጽ​መው ጠፉ።


ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


እር​ስ​ዋም፥ “ወዳ​ጆች የሰ​ጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለ​ች​ውን ሁሉ ወይ​ን​ዋ​ንና በለ​ስ​ዋን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ይሆኑ ዘንድ አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊ​ትና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ይበ​ሉ​ታል።


ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል።


“ሌላ ምሳሌ ስሙ። የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ትን ብታ​ወጣ ግን የተ​ጣ​ለች ናት፤ ለመ​ር​ገ​ምም የቀ​ረ​በች ናት፤ ፍጻ​ሜ​ዋም ለመ​ቃ​ጠል ይሆ​ናል።


跟着我们:

广告


广告