Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ታዲያ፥ ይህ ሕፃን በጎውን ከክፉ ለይቶ ከማወቁ በፊት አንተ ትፈራቸው የነበሩ የእነዚህ የሁለት ነገሥታት ምድሮች ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሕፃኑም ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 7:16
12 交叉引用  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።


ብታ​ም​ን​በት ይቀ​ድ​ስ​ሃል፤ እንደ ድን​ጋይ ዕን​ቅ​ፋ​ትም አያ​ደ​ና​ቅ​ፍ​ህም፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ድጥ ዓለ​ትም አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ቤቶች ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጥ​መ​ድና በአ​ሽ​ክላ ተይ​ዘው ይኖ​ራሉ።


ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን የኤ​ፍ​ሬ​ምን ዘር ሁሉ፥ እንደ ጣልሁ፥ እን​ዲሁ ከፊቴ እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


እኔ ኤፍ​ሬ​ምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከእኔ አል​ራ​ቀም፤ ኤፍ​ሬም ዛሬ አመ​ን​ዝ​ሮ​አ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አ​ልና።


ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ።


እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።


ደግሞ፦ ይማ​ረ​ካሉ ያላ​ች​ኋ​ቸው ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ዛሬም መል​ካ​ሙን ከክፉ መለ​የት የማ​ይ​ችሉ ሕፃ​ኖ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባሉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለእ​ነ​ርሱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይወ​ር​ሱ​አ​ታ​ልም።


跟着我们:

广告


广告