Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 65:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የወ​ይን ፍሬ በዘ​ለ​ላው በተ​ገ​ኘች ጊዜ፦ በረ​ከት በእ​ር​ስዋ ላይ አለና አታ​ጥ​ፉት እን​ደ​ሚ​ባ​ለው፥ ሁሉን እን​ዳ​ላ​ጠፋ ስለ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ ሰዎችም፣ ‘በውስጡ በረከት ስላለ አትቍረጡት’ እንደሚሉ፣ እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወይን ጠጅ ከወይን ዘለላ እንደሚገኝና ‘በረከት ስላለበት አታጥፉት’ እንደሚባል እኔም በዚሁ ዐይነት ስለ አገልጋዮቼ ስል ሕዝቡን በሙሉ አላጠፋም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፦ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፉት እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ ባሪያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 65:8
14 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “በሰ​ዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድ​ቃን ባገኝ ከተ​ማ​ውን ሁሉ ስለ እነ​ርሱ አድ​ና​ለሁ።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ቅሬታ በኀ​ያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ናሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀ​ሩት ይድ​ናሉ።


ስለ ስሜ ቍጣ​ዬን አሳ​ይ​ሃ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ህም ግር​ማ​ዬን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።


በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ዐሥ​ረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ቅጠ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በረ​ገፉ ጊዜ እንደ ግራ​ርና እንደ ኮም​በል ዛፍ ሁነው ይቀ​ራሉ።


አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።


ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።


跟着我们:

广告


广告