Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 64:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከጥንት ጀምሮ፣ በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣ ከአንተ በቀር አምላክ እንዳለ ያየ ዐይን የለም፤ የሰማም ጆሮ የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 64:4
36 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያድ​ነው ዘንድ ይጠ​ብ​ቃል።


ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን።


ረጃ​ጅም ተራ​ራ​ዎች ለዋ​ሊ​ያ​ዎች፥ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለአ​ሽ​ኮ​ኮ​ዎች መሸሻ ናቸው።


አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለሁ፤ ነፍሴ አን​ተን ተጠ​ማች፥ እን​ጨ​ትና ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ሥጋ​ዬን ለአ​ንተ እን​ዴት ልዘ​ር​ጋ​ልህ


በዚ​ያም ቀን፥ “እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድ​ር​ገ​ነ​ዋል፤ ያድ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ ነው፤ ጠብ​ቀ​ነ​ዋል፤ በመ​ዳ​ና​ች​ንም ደስ ይለ​ናል፤ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን” ይላሉ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ዐመ​ፃ​ችን በአ​ንተ ፊት በዝ​ቶ​አ​ልና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም መስ​ክ​ሮ​ብ​ና​ልና፥ ዐመ​ፃ​ችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም አላ​ወ​ቅ​ን​ምና።


ከቶ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርን ማን ሰም​ቶ​አል? እን​ዲ​ህስ ያለ ነገ​ርን ማን አይ​ቶ​አል? በውኑ ሀገር በአ​ንድ ቀን ታም​ጣ​ለ​ችን? ወይስ በአ​ንድ ጊዜ ሕዝብ ይወ​ለ​ዳ​ልን? ጽዮን እን​ዳ​ማ​ጠች ወዲ​ያው ልጆ​ች​ዋን ወል​ዳ​ለ​ችና።


ሁሉም እንደ ምድጃ ግለ​ዋል፤ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል የሚ​ጠ​ራኝ የለም።


በአሕዛብም መካከል ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ ይመለሱማል።


ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የአባቴ ቡሩካን! ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስሙ ስም​ዖን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ጻድ​ቅና ደግ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ደስ​ታ​ቸ​ውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደ​ርግ ነበር፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስም ያደ​ረ​በት ነበር።


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


የዓ​ለም ተስ​ፋው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ መም​ጣት ይጠ​ባ​በቅ ነበ​ርና።


ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም መም​ጣት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ችሁ ፍጹም ጸጋን እን​ዳ​ታጡ፥


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


አሁን ግን፥ በሰ​ማ​ያት ያለ​ች​ውን የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሀገር ተስፋ ያደ​ርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ አያ​ፍ​ርም፤ ተስፋ ያደ​ረ​ጉ​አ​ትን ሀገር አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።


ፍቅርም እንደዚህ ነው። እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።


跟着我们:

广告


广告