Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 63:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋራ አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቷል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ይመልሳል “እኔ ብቻዬን አሕዛብን ሁሉ እንደ ወይን ረገጥኩ፤ ይህን በማደርግበት ጊዜ ከሕዝቦች ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም፤ እኔ በቊጣዬ ረገጥኳቸው፤ በመዓቴም አደቀቅኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጨ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፥ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸዋም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 63:3
18 交叉引用  

አህ​ያ​ይ​ቱን በወ​ይን ግንድ ያስ​ራል፤ የአ​ህ​ያ​ይ​ቱ​ንም ግል​ገል በወ​ይን ሐረግ፤ ልብ​ሱን በወ​ይን ያጥ​ባል፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም በዘ​ለ​ላው ደም።


እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።


ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ገው፤ ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም በአ​ንድ ጊዜ አጥ​ፋ​ቸው።


ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሁ​ከ​ትና የጥ​ፋት፥ የመ​ረ​ገ​ጥና የስ​ብ​ራ​ትም ቀን በጽ​ዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖ​አል። ታና​ሹና ታላ​ቁም ሸሽ​ተው በተ​ራራ ላይ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጠ​ናል፤ እህ​ልም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ጭድም በጭቃ እን​ደ​ሚ​በ​ራይ እን​ዲሁ ሞዓብ ይረ​ገ​ጣል።


የኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል በእ​ጅና በእ​ግር ይረ​ገ​ጣል፤


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አፈ​ሰ​ስ​ሁት።


ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”


ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።


በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告