ኢሳይያስ 63:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 አብርሃም ባያውቀን፣ እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳ፣ አንተ እኮ አባታችን ነህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ ከጥንትም ቢሆን ስምህ “ቤዛችን” ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ ጌታ አንተ አባታችን ነህ፤ ስምህም ከዘለዓለም ታዳጊያችን ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤል ባይቀበለንም እንኳ አንተ አባታችን ነህ፤ አምላክ ሆይ! ስምህ ከጥንት እንደ ሆነ ሁሉ አንተ አባታችን ነህ፤ አንተ ታዳጊአችን ነህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፥ አቤቱ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው። 参见章节 |