ኢሳይያስ 60:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ የተርሴስም መርከቦች አስቀድመው ይመጣሉ፤ ልጆችሽ ስለ ከበረው ስለ እስራኤል ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ስም ወርቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣ የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለጌታ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ፥ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ለማምጣት፥ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል። 参见章节 |