Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 60:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የተ​ተ​ው​ሽና የተ​ጠ​ላሽ ሆነ​ሻ​ልና የሚ​ረ​ዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታን ለልጅ ልጅ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣ እኔ የዘላለም ትምክሕት፣ የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ከዚህ በፊት የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሽ ማንም በአንቺ በኩል የማያልፍ የነበረ ቢሆንም እንኳ፥ የዘለዓለም መመኪያና በየትውልዱ ሁሉ መደሰቻ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፥ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 60:15
20 交叉引用  

ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።


እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለኝ፥ “ከተ​ሞች የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አጥ​ተው እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ ቤቶ​ችም ሰው አልቦ እስ​ኪ​ሆኑ፥ ምድ​ርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስ​ክ​ት​ቀር ድረስ ነው፤”


ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን ያር​ቃል፤ በም​ድ​ርም የቀ​ሩት ይበ​ዛሉ።


ሌላ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ደስታ አላ​ቸው።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “የተ​ተ​ወች” አት​ባ​ዪም፤ ምድ​ር​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አት​ባ​ልም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንቺ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ ምድ​ር​ሽም ባል ታገ​ባ​ለ​ችና አንቺ፥ “ደስ​ታዬ የሚ​ኖ​ር​ባት” ትባ​ያ​ለሽ፤ ምድ​ር​ሽም፥ “ባል ያገ​ባች” ትባ​ላ​ለች።


ነገር ግን በው​ስ​ጥዋ ደስ​ታ​ንና ሐሤ​ትን ያገ​ኛሉ፤ እኔም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደስ​ታን ለሕ​ዝ​ቤም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


እኔ ከክፉ ቍስ​ልሽ እፈ​ው​ስ​ሻ​ለሁ፤ ጤና​ሽን እመ​ል​ስ​ል​ሻ​ለሁ፤ ቍስ​ል​ሽ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ማንም የማ​ይ​ሻት፥ የተ​ጣ​ለች ጽዮን ብለው ጠር​ተ​ው​ሻ​ልና።”


የሐ​ሤት ድም​ፅና የደ​ስታ ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽራ ድም​ፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​መጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰ​ማል። የዚ​ያ​ችን ምድር ምር​ኮ​ኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


跟着我们:

广告


广告