Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 59:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ፍር​ድን ከመ​ከ​ተል ወደ ኋላ ርቀ​ናል፤ ጽድ​ቅም በሩቅ ቆሞ​አል፤ እው​ነ​ትም ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ታጥ​ቶ​አል፤ በቀና መን​ገ​ድም መሄድ አል​ቻ​ሉም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ፍትህም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሕዝብ አደባባይ እውነት ስለ ተሰናከለና ታማኝነት ሊገባ ስላልቻለ ፍትሕ ወደ ኋላ ተመልሶአል፤ ጽድቅም ተዳክሞአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፥ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 59:14
25 交叉引用  

ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መልሶ፥ “ይሁን፤ ይህ ጐባጣ እንደ ቀና አይ​መካ” ብሎ መለሰ።


ደግ​ሞም ከፀ​ሐይ በታች በጻ​ድቅ ስፍራ ኃጥእ፥ በኃ​ጥ​እም ስፍራ ጻድቅ እን​ዳለ አየሁ።


ፍርድ መል​ቶ​ባት የነ​በረ የታ​መ​ነ​ች​ይቱ የጽ​ዮን ከተማ እን​ዴት ጋለ​ሞታ ሆነች! ጽድቅ አድ​ሮ​ባት ነበር፤ አሁን ግን ወን​በ​ዴ​ዎ​ችና ነፍሰ ገዳ​ዮች አሉ​ባት።


እና​ንተ ከጽ​ድቅ የራ​ቃ​ችሁ ልበ ጥፉ​ዎች፥ ስሙኝ፤


በደ​ለ​ኛ​ውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ የጻ​ድ​ቁ​ንም ጽድቅ ለሚ​ያ​ስ​ወ​ግ​ዱ​በት ወዮ​ላ​ቸው!


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።


እንደ ድብና እንደ ርግብ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ፍር​ድን እን​ጠ​ባ​በቅ ነበር፤ መዳ​ንም የለም፤ ከእ​ኛም ርቆ​አል።


ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።


ስለ​ዚህ ፍርድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርቆ​አል፤ ጽድ​ቅም አላ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ ብር​ሃ​ንን ሲጠ​ባ​በቁ ብር​ሃ​ና​ቸው ጨለማ ሆነ​ባ​ቸው፤ ብር​ሃ​ን​ንም ሲጠ​ባ​በቁ በጨ​ለማ ሄዱ፤


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


በሐ​ሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ሌባም ገብ​ቶ​አ​ልና፥ በው​ጭም ወን​በ​ዴ​ዎች ቀም​ተ​ዋ​ልና እስ​ራ​ኤ​ልን እፈ​ውስ ዘንድ በወ​ደ​ድሁ ጊዜ የኤ​ፍ​ሬም ኀጢ​አ​ትና የሰ​ማ​ርያ ክፋት ተገ​ለጠ።


ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል።


ፍር​ድን ወደ ቍጣ፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ፍሬ ወደ እሬት ለው​ጣ​ች​ኋ​ልና፥ በውኑ ፈረ​ሶች በጭ​ንጫ ላይ ይሮ​ጣ​ሉን? ወይስ በሬ​ዎች በዚያ ላይ ያር​ሳ​ሉን?


ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፣ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፣ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።


跟着我们:

广告


广告