Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 59:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዐመ​ፃ​ችን በአ​ንተ ፊት በዝ​ቶ​አ​ልና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም መስ​ክ​ሮ​ብ​ና​ልና፥ ዐመ​ፃ​ችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም አላ​ወ​ቅ​ን​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በደላችን በፊትህ በዝቷል፤ ኀጢአታችን መስክሮብናል፤ በደላችን ከእኛ አልተለየም፤ ዐመፀኝነታችንንም እናውቃለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “በደላችን በአንተ ፊት ብዙ መሆኑን ኃጢአታችን በእኛ ላይ ይመሰክራል፤ ሁልጊዜ እንበድላለን፤ መበደላችንንም እናውቃለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 59:12
31 交叉引用  

ስለ ክፉ ሥራ​ች​ንና ስለ ታላቁ በደ​ላ​ችን ካገ​ኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት አል​ቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ንም፤ ነገር ግን ድኅ​ነ​ትን ሰጠ​ኸን።


እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ኀጢ​አ​ታ​ችን በራ​ሳ​ችን ላይ በዝ​ቶ​አ​ልና፥ በደ​ላ​ች​ንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ​አ​ልና አም​ላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ራ​ማ​ለሁ።


በደ​ረ​ሰ​ብ​ንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ አንተ እው​ነት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ እኛም እጅግ በድ​ለ​ና​ልና።


ከመ​ል​ካም ይልቅ ክፋ​ትን፥ ጽድ​ቅ​ንም ከመ​ና​ገር ይልቅ ዐመ​ፃን ወደ​ድህ።


ኀጢ​አ​ተኛ ወገ​ንና ዐመፅ የተ​ሞ​ላ​በት ሕዝብ፥ የክ​ፉ​ዎች ዘር፥ በደ​ለ​ኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮ​ላ​ችሁ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዋ​ች​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።


ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።


አቤቱ! ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዙ ነውና፥ በአ​ን​ተም ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና ኀጢ​አ​ታ​ችን ተቃ​ው​ሞ​ናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድ​ርግ።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አቅ​ን​ተሽ አንሺ፤ ያል​ተ​ጋ​ደ​ም​ሽ​በት ስፍራ እን​ዳ​ለም ተመ​ል​ከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራ​ዎች በመ​ን​ገድ ላይ ተቀ​ም​ጠሽ በዝ​ሙ​ት​ሽና በክ​ፋ​ትሽ ምድ​ሪ​ቱን አር​ክ​ሰ​ሻ​ታ​ልና።


እር​ስ​ዋም ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ፍር​ዴን በኀ​ጢ​አት ለወ​ጠች፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ከአሉ ሀገ​ሮች ሁሉ ይልቅ ትእ​ዛ​ዜን ተላ​ለ​ፈች፤ ፍር​ዴን ጥለ​ዋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዱ​ምና።


ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


“ምድር በአ​ሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች፥ ከተ​ማም በኀ​ጢ​አት ተመ​ል​ታ​ለ​ችና ሰን​ሰ​ለት ሥራ።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ትዕ​ቢት በፊቱ ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤ​ልና ኤፍ​ሬም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ፤ ይሁ​ዳም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይደ​ክ​ማል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውር​ደ​ቱና ስድቡ በፊቱ ነው፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሱም፤ በዚ​ህም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ለ​ጉ​ትም።


ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፥ ፍርድም ድል ነሥቶ አይወጣም፣ ኃጢአተኛ ጻድቅን ይከብባልና፣ ስለዚህ ፍርድ ጠማማ ሆኖ ይወጣል።


እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告