Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 53:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋራ እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋራ ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ ከክፉ አድራጊዎችም ጋራ በመቈጠሩ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕይወቱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፤ ከክፉ አድራጊዎችም ጋር ተቈጠረ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የብዙዎችን ኃጢአት ተሸከመ፤ ለበደለኞችም ማለደ፤ ስለዚህ እኔ ከታላላቆቹ ጋር ድርሻ እንዲኖረውና ከኀያላን ጋር ምርኮን እንዲካፈል አደርገዋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፥ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፥ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 53:12
38 交叉引用  

በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


“አሁ​ንም ነፍሴ በው​ስጤ ፈሰ​ሰች፤ ጭን​ቀ​ትም በእኔ ላይ ሞላ፤


ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ጠላ​ትም፦ ‘አሳ​ድጄ እይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምር​ኮም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም አጠ​ግ​ባ​ታ​ለሁ፤ በሰ​ይ​ፌም እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በእ​ጄም እገ​ዛ​ለሁ’ አለ።


እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።


እነሆ፥ አገ​ል​ጋዬ ያስ​ተ​ው​ላል፤ ከፍ ከፍ ይላል፥ ይከ​ብ​ራ​ልም፤ እጅ​ግም ደስ ይለ​ዋል።


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እር​ሱን ያደ​ን​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም አፋ​ቸ​ውን ይዘ​ጋሉ፤ ስለ እርሱ ያል​ተ​ወ​ራ​ላ​ቸው ያው​ቁ​ታ​ልና፥ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታ​ልና።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።


ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና “አባቴ! ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን፤” አለ።


ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።


መጽሐፍም “ከዐመፀኞች ጋር ተቆጠረ፤” ያለው ተፈጸመ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።”


ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


የሚ​ፈ​ር​ድስ ማነው? የሞ​ተው፥ ይል​ቁ​ንም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀኝ የተ​ቀ​መ​ጠው፥ ደግሞ ስለ እና የሚ​ፈ​ር​ደው ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤


አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


ዘወ​ትር በእ​ርሱ በኩል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​ቡ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው ይቻ​ለ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ነውና ያስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ዋል።


ክር​ስ​ቶስ በእጅ ወደ ተሠ​ራች የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ምሳሌ ወደ​ም​ት​ሆን ቅድ​ስት አል​ገ​ባ​ምና፥ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እር​ስዋ ወደ ሰማይ ገባ።


ይህስ ባይ​ሆን ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓ​ለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመ​ሠ​ዋት ኀጢ​አ​ትን ይሽ​ራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገ​ለጠ።


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።


ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告