Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 52:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ፥ አገ​ል​ጋዬ ያስ​ተ​ው​ላል፤ ከፍ ከፍ ይላል፥ ይከ​ብ​ራ​ልም፤ እጅ​ግም ደስ ይለ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ አገልጋዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አገልጋዬ ሥራው ሁሉ ይከናወንለታል፤ በክብርም እጅግ ከፍ ከፍ ይላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፥ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 52:13
22 交叉引用  

እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አንተ ባር​ያዬ ነህ፤ በአ​ን​ተም እከ​በ​ራ​ለሁ” አለኝ።


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን የሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳን አድሮ የሚ​ኖር፥ ለተ​ዋ​ረ​ዱት ትዕ​ግ​ሥ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ልባ​ቸ​ውም ለተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


በላ​ያ​ቸ​ውም አንድ እረኛ አቆ​ማ​ለሁ፤ እር​ሱም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል፤ እር​ሱም ባሪ​ያዬ ዳዊት ነው፤ እረ​ኛም ይሆ​ና​ቸ​ዋል።


ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ከላይ የመ​ጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከም​ድር የተ​ገ​ኘ​ውም ምድ​ራዊ ነው፤ የም​ድ​ሩ​ንም ይና​ገ​ራል፤ ከሰ​ማይ የመ​ጣው ግን ከሁሉ በላይ ነው።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


跟着我们:

广告


广告