Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በጥ​ዋት ወደ መሸታ ቤት ለሚ​ገ​ሠ​ግ​ሡና በመ​ጠጥ ቤት ለሚ​ውሉ ወዮ​ላ​ቸው! ወይኑ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፣ እስኪያነድዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፤ እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ጠጥተው ለመስከር ማልደው ወደ መሸታ ቤት ለሚገሠግሡ፥ የወይን ጠጅ እስኪያቃጥላቸው ሌሊቱንም ሁሉ በዚያው መቈየት ለሚፈልጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስካርን ለመከተል በጥዋት ለሚማልዱ፥ የወይን ጠጅም እስኪያቃጥላቸው እስከ ሌሊት ድረስ ለሚዘገዩ ወዮላቸው!

参见章节 复制




ኢሳይያስ 5:11
21 交叉引用  

ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?


ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።


በመጨረሻም እባብ እንደ ነደፈው፥ የእፉኝትም መርዝ እንደ ተሰራጨበት ትዘረጋለህ።


እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።


ወይ​ንን የሚ​ጠ​ጡት አፈሩ፤ የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም ለሚ​ጠ​ጡት መራራ ሆነ።


ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


የኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል በእ​ጅና በእ​ግር ይረ​ገ​ጣል፤


የወ​ይን ጠጅ ለሚ​ጠጡ ኀያ​ላን፥ የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ው​ንም መጠጥ ለሚ​ደ​ባ​ልቁ ጽኑ​ዓን ወዮ​ላ​ቸው!


ኑ፤ የወ​ይን ጠጅ እን​ው​ሰድ፤ በሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ እን​ርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እን​ዲሁ ነገ ይሆ​ናል፤ ከዛ​ሬም ይልቅ እጅግ ይበ​ል​ጣል ይላሉ።


ኅፍረተ ሥጋውን ለማየት ባልንጀራውን ለሚያጠጣ፥ ክፉንም ለሚጨምርበት፥ ለሚያሰክረውም ወዮለት!


እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


ሌቦች፥ ወይም ቀማ​ኞች፥ ወይም ሰካ​ሮች፥ ወይም ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ወይም ነጣ​ቂ​ዎች፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ሱ​አ​ትም።


አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።


跟着我们:

广告


广告