ኢሳይያስ 49:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 አጥተሻቸው የነበሩት ልጆችሽም በጆሮሽ፦ ስፍራ ጠብቦናልና የምንቀመጥበት ቦታ አስፊልን ይላሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 በሐዘንሽ ዘመን የወለድሻቸው ልጆች፣ ጆሮሽ እየሰማ፣ ‘ይህ ቦታ በጣም ጠብቦናል፤ የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይሉሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ በጆሮሽ፦ “ስፍራ ጠብቦኛልና እድንቀመጥ ቦታ አስፊልን” ይላሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 በስደት የተወለዱ ልጆችሽ ‘ይህ ቦታ ለእኛ በጣም ጠባብ ስለ ሆነ የምንኖርበት ሰፊ ቦታ ስጪን’ ይሉሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ በጆሮሽ፦ ስፍራ ጠብቦኛልና እቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልኝ ይላሉ። 参见章节 |