Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 49:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እነሆ፥ እነ​ዚህ ከሩቅ፥ እነ​ሆም፥ እነ​ዚህ ከሰ​ሜ​ንና ከም​ዕ​ራብ፥ እነ​ዚ​ህም ከፋ​ርስ ሀገር ይመ​ጣሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነሆ፤ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ አንዳንዶች ከሰሜን ሌሎች ከምዕራብ፣ የቀሩት ደግሞ ከሲኒም ይመጣሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ። እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝቦቼ ከሩቅ አገሮች ይመጣሉ፤ ከሰሜንና ከምዕራብ እንዲሁም ከሲኒም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ። እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 49:12
24 交叉引用  

ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥


ለአ​ሕ​ዛ​ብም ምል​ክ​ትን ያቆ​ማል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የቀ​ሩ​ትን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከይ​ሁ​ዳም የተ​በ​ተ​ኑ​ትን ከአ​ራቱ የም​ድር ማዕ​ዘ​ኖች ያከ​ማ​ቻል።


እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነ​ዚ​ህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለ​ብ​ሻ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ እንደ ሙሽ​ራም ትጐ​ና​ጸ​ፊ​አ​ቸ​ዋ​ለሽ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ ይጠ​ሩ​ሃል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አክ​ብ​ሮ​ሃ​ልና ስለ አም​ላ​ክህ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ በአ​ንተ ይማ​ጠ​ናሉ።


በም​ዕ​ራብ ያሉት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም፥ በፀ​ሐይ መው​ጫም ያሉት ክብ​ሩን ይፈ​ራሉ። መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ኀይ​ለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመ​ጣል።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ ልጆ​ች​ሽም እንደ ተሰ​በ​ሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ከሩቅ ይመ​ጣሉ፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ንቃ ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል።


“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።


ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።


በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።


በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።


እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤


ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከሰ​ሜ​ንና ከደ​ቡብ ይመ​ጣሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት በማ​ዕድ ይቀ​መ​ጣሉ፤


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


跟着我们:

广告


广告