Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 45:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሰማያትን የፈጠረ፣ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያበጃት፣ የሠራት፣ የመሠረታት፣ የሰው መኖሪያ እንጂ፣ ባዶ እንድትሆን ያልፈጠራት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሰማያትን የፈጠረ ጌታ፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 45:18
16 交叉引用  

በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ።


ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ሰውን በአ​ር​ኣ​ያ​ች​ንና በአ​ም​ሳ​ላ​ችን እን​ፍ​ጠር፤ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ምድ​ርን ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትን ሁሉ ይግዛ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤


እኔ ምድ​ርን ሠር​ቻ​ለሁ፤ ሰው​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ቼ​አ​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አዝ​ዣ​ለሁ።


እጄም ምድ​ርን መሥ​ር​ታ​ለች፤ ቀኜም ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ታ​ለች፤ እጠ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም መጥ​ተው ይቆ​ማሉ።


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።


ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ የመ​ሠ​ረተ፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።


跟着我们:

广告


广告