Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 45:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ቂሮስን ለጽድቅ ሥራ አነሣሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም አቀናለታለሁ፤ ከተማዬን ኢየሩሳሌምን እንደገና ይሠራታል፤ በስደት ላይ ያሉ ሕዝቤንም ነጻ ያወጣል፤ ይህንንም የሚያደርገው ማንም ገንዘብ እንዲከፍለው ወይም ውለታውን እንዲመልስለት አይደለም።” የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሮአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፥ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 45:13
19 交叉引用  

ከሕ​ዝቡ ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ረው አም​ላክ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ይሥራ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።


በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


እነሆ፥ ብር የማ​ይ​ሹ​ትን፥ ወር​ቅም የማ​ያ​ም​ራ​ቸ​ውን ሜዶ​ና​ው​ያ​ንን በእ​ና​ንተ ላይ አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


ዓለ​ሙን ሁሉ ባድማ ያደ​ረገ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ያፈ​ረሰ፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ቤታ​ቸው ያል​ሰ​ደደ ሰው ይህ ነውን?


ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።


ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።


“እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በጽ​ድቅ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ጄም እይ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብር​ሃን አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


“በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ዝቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የና​ሱ​ንም ደጆች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤


ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከ​ር​ሁት ምክር ዎፍን እጠ​ራ​ለሁ፤ ተና​ገ​ርሁ፤ አመ​ጣ​ሁም፤ ፈጠ​ርሁ፤ አደ​ረ​ግ​ሁም፤ አመ​ጣ​ሁት፤ መን​ገ​ዱ​ንም አቀ​ና​ሁ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በኀ​ያ​ላን የተ​ማ​ረኩ ይወ​ሰ​ዳሉ፤ የጨ​ካ​ኞ​ችም ብዝ​በዛ ያመ​ል​ጣል፤ እኔም ፍር​ድ​ሽን እፈ​ር​ድ​ል​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም አድ​ና​ለሁ።


ሕዝቤ በከ​ንቱ ተወ​ስ​ዶ​አ​ልና አሁን ከዚህ ምን አቆ​ማ​ችሁ?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትጮ​ሃ​ላ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስሜም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ሁል​ጊዜ ይሰ​ደ​ባል።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


跟着我们:

广告


广告