Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 45:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ለቀባሁት፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት፣ ነገሥታትን ትጥቅ አስፈታ ዘንድ፣ ሕዝብን ሁሉ ላስገዛለት፣ ደጆች እንዳይዘጉ፣ በሮቹን በፊቱ ለምከፍትለት፣ ለቂሮስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ ለቀባው፥ አሕዛብንም በፊቱ እንዲገዙለት፥ የነገሥታትንም ወገብ እዲፈታ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹ በፊቱ እንዲከፈቱለት፥ ቀኝ እጁን ለያዘው ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦

参见章节 复制




ኢሳይያስ 45:1
31 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ሂድ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ በም​ድረ በዳ ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለስ፤ ከዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አዛ​ሄ​ልን ቅባው፤


በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ እር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ አዋጅ አስ​ነ​ገረ፤ ደግ​ሞም በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ አለ፦


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤


በአ​ለ​ቆች ላይ ውር​ደ​ትን ያመ​ጣል፥ ትሑ​ታ​ን​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።


የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ቃል አት​ርሳ፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ኵራት ሁል​ጊዜ ወደ አንተ ይውጣ።


ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ።


እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።


ቀኝ እጅ​ህን የያ​ዝ​ሁህ፥ እን​ዲ​ህም የም​ልህ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና።


ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።


ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።


“እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በጽ​ድቅ ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ጄም እይ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለ​ሁም፤ ለልጅ ልጅ ቃል ኪዳን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብር​ሃን አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


እኔ ራሴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ፤ አም​ጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱም ትከ​ና​ወ​ን​ለ​ታ​ለች።


አሁ​ንም ምድ​ርን ሁሉ ለባ​ሪ​ያዬ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ለሁ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ዘንድ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።


ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።


ሰይፍ በከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንና በባ​ቢ​ሎን በሚ​ኖሩ ላይ፥ በመ​ሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋና በጥ​በ​በ​ኞ​ችዋ ላይ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”


ስለ እኔ ሠር​ተ​ዋ​ልና በጢ​ሮስ ላይ ስለ አገ​ለ​ገ​ለው አገ​ል​ግ​ሎት የግ​ብ​ፅን ምድር ደመ​ወዝ አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የወንዞቹም መዝጊያዎች ተከፈቱ፥ የንጉሡ ቤትም ቀለጠች።


እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።


跟着我们:

广告


广告