Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 44:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አያ​ው​ቁም፤ አያ​ስ​ቡም፤ እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልቦ​ቻ​ቸው ተጋ​ር​ደ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምንም አያውቁም፤ አያስተውሉም፤ እንዳያዩ ዐይናቸው ተሸፍኗል፤ እንዳያስተውሉ ልባቸው ተዘግቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዐይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉም ልቦቻቸውን ጨፍነዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደዚህ ያሉት ሰዎች ዐይኖቻቸው ስለ ተሸፈኑ ማየት አይችሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አያውቁም፥ አያስቡም፥ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉም ልቦቻቸውን ጨፍነዋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 44:18
34 交叉引用  

በሬ ገዢ​ውን አህ​ያም የጌ​ታ​ውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስ​ራ​ኤል ግን አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ሕዝ​ቤም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ኝም።”


አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።


ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ን​ቅ​ልፍ መን​ፈ​ስን አፍ​ስ​ሶ​ባ​ቸ​ዋል፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን፥ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ዐይን፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያዩ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ዐይን ጨፍ​ኖ​ባ​ቸ​ዋል።


ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም።


እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።


ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ቀ​ርጹ ያን​ጊዜ አይ​ኖ​ሩም፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል የሚ​ሠ​ሩም ሁሉ ከን​ቱ​ዎች ናቸው፤ የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን የራ​ሳ​ቸ​ውን ፍላ​ጎት የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው።


እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።


“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


እን​ግ​ዲህ ቃሌን ለምን አታ​ስ​ተ​ው​ሉም? ቃሌን መስ​ማት ስለ​ማ​ት​ችሉ ነው።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ በቀ​ድሞ ዘመን እንደ ነበ​ሩ​በት እንደ ጠባ​ያ​ቸው ሊኖሩ ተዋ​አ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告