Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 43:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እኔ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ የሚ​ያ​ድን አም​ላክ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እኔ፥ እኔ ጌታ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 43:11
28 交叉引用  

ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።


እነሆ፥ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒቴ ነው፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሬና ዝማ​ሬዬ ነው፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ሆኖ​አ​ልና በእ​ርሱ ታም​ኜ​አ​ለሁ፤ አል​ፈ​ራ​ምም።”


ይህም ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ይሆ​ናል፤ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው የተ​ነሣ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጮ​ኻ​ሉና፥ እር​ሱም የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውን ሰው ይል​ክ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ዳል፤ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብ​ሬን ለሌላ፥ ምስ​ጋ​ና​ዬ​ንም ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች አል​ሰ​ጥም።


እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”


የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ወተት ትጠ​ጫ​ለሽ፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ብል​ጽ​ግና ትበ​ያ​ለሽ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ።


ነገር ግን የይ​ሁ​ዳን ልጆች ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ በቀ​ስት ወይም በሰ​ይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠ​ረ​ገላ፥ ወይም በፈ​ረ​ሶች፥ ወይም በፈ​ረ​ሰ​ኞች የማ​ድ​ና​ቸው አይ​ደ​ለም” አለው።


ሰማ​ይን ያጸ​ናሁ፥ ምድ​ር​ንም የፈ​ጠ​ርሁ፥ እጆ​ችም የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትን ያቆሙ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። እን​ዳ​ት​ከ​ተ​ላ​ቸ​ውም እነ​ር​ሱን አላ​ሳ​የ​ሁ​ህም። ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ አት​ወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚ​ያ​ድ​ንህ የለ​ምና።


እኔ ግን ከም​ስ​ጋ​ናና ከኑ​ዛዜ ቃል ጋር እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤ የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ ሆይ! የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ለአ​ንተ እከ​ፍ​ላ​ለሁ።”


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ልቡ​ና​ዬም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች።


እነሆ፥ ዛሬ በዳ​ዊት ከተማ መድ​ኅን ተወ​ል​ዶ​ላ​ች​ኋል፤ ይኸ​ውም ቡሩክ ጌታ ክር​ስ​ቶስ ነው።


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።


ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告