Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 42:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዝም እላ​ለ​ሁን? አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እታ​ገ​ሣ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም እጨ​ር​ሳ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ለረዥም ጊዜ ዝም አልሁ፤ ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጮኻለሁ፤ ቍና ቍና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለረጅም ጊዜ ታገሥኩ፤ ጸጥ ብዬም ራሴን ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት ከፍተኛ ድምፅ አሰማለሁ፤ የቊጣ እስትንፋስ እተነፍሳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፥ አሁን ምጥ እንደያዛት ሴት እጮኻለሁ፥ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 42:14
16 交叉引用  

እኔ ቃል ተሞ​ል​ቻ​ለ​ሁና፥ በው​ስ​ጤም ያለ መን​ፈስ አስ​ጨ​ን​ቆ​ኛ​ልና።


ጥቂት እን​ድ​ተ​ነ​ፍስ እና​ገ​ራ​ለሁ። ከን​ፈ​ሬ​ንም ገልጬ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥ ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


ሐሰት የተ​ና​ገ​ር​ሽው፥ እኔ​ንም ያላ​ሰ​ብ​ሽው፥ በል​ብ​ሽም ነገ​ሩን ያላ​ኖ​ር​ሽው ማንን ሰግ​ተሽ ነው? ማን​ንስ ፈር​ተሽ ነው? እኔም ዝም አል​ሁሽ፤ አን​ቺም አል​ፈ​ራ​ሽ​ኝም።


አቤቱ፥ በዚህ ነገር ሁሉ ታገ​ሥ​ኸን፤ ዝም አል​ኸን፤ እጅ​ግም አዋ​ረ​ድ​ኸን።


እነሆ፥ በፊቴ ተጽ​ፎ​አል፦ ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት በአ​ንድ ላይ ወደ ብብ​ታ​ቸው ፍዳ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለሁ እንጂ ዝም አል​ልም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


አንቺ እኔን ከድ​ተ​ሽ​ኛል፤ እኔ​ንም መከ​ተል ትተ​ሻል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ ኋላ​ሽም ተመ​ል​ሰ​ሻል፤ ስለ​ዚህ እጄን በአ​ንቺ ላይ ዘር​ግቼ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ይቅ​ርም አል​ላ​ቸ​ውም።


እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሥ​ራ​ች​ሁን ክፋ​ትና ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ርኵ​ሰት ይታ​ገሥ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚህ ምድ​ራ​ችሁ ባድማ፥ በረ​ሃና መረ​ገ​ሚያ ሆና​ለች፤ እስከ ዛሬም የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊት ወደ እርሱ ለሚ​ጮኹ ለወ​ዳ​ጆቹ አይ​ፈ​ር​ድ​ምን? ወይስ ቸል ይላ​ቸ​ዋ​ልን?


የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፤


跟着我们:

广告


广告