Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 41:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በመ​ጀ​መ​ሪያ ለጽ​ዮን፦ ግዛ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ወደ መን​ገ​ድዋ እመ​ል​ሳ​ታ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በመጀመሪያ፣ ‘እነሆ፤ ተመልከቺአቸው!’ ብዬ ለጽዮን የተናገርሁ እኔ ነበርሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን ሰጥቻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነሆ ተመልከች፥ እላለሁ፤ ለእየሩሳሌምም የምሥራች ነጋሪን እሰጣለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በመጀመሪያ ይህን ዜና ለጽዮን የገለጥኩላት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም መልካም ዜና አብሣሪ የላክሁላት እኔ ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ፥ ለእየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 41:27
14 交叉引用  

ለጽ​ዮን የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ከፍ ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ድም​ፅ​ህን በኀ​ይል አንሣ፤ አት​ፍራ፤ ለይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ! ብለህ ንገር።


ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።


ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


እኔ አም​ላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለ​ምና የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የጥ​ን​ቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የጠ​ራ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ፊተ​ኛው ነኝ፤ እኔም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነኝ።


የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።


ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


“መል​ካ​ሙን የም​ሥ​ራች የሚ​ያ​ወሩ እግ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዴት ያማሩ ናቸው?” ተብሎ እንደ ተጻፈ ካል​ተ​ላኩ እን​ዴት ይሰ​ብ​ካሉ?


“በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦


跟着我们:

广告


广告