Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 40:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ያዕ​ቆብ ሆይ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ መን​ገዴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተሰ​ው​ራ​ለች፤ አም​ላ​ኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍር​ዴ​ንም ትት​ዋል፤ ለምን ትላ​ለህ? ለም​ንስ እን​ዲህ ትና​ገ​ራ​ለህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ያዕቆብ ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትላለህ? እስራኤል ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትናገራለህ? “መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ “መንገዴ ከጌታ ተሰውራለች፥ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! “አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤ መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤” ብለህ ለምን ታማርራለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ መንገድህ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 40:27
10 交叉引用  

ስለ​ዚ​ህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰ​ልሁ፤ በተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም ጊዜ አሰ​ብ​ሁት።


“እን​ደ​ዚህ የፈ​ረ​ደ​ብኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ነፍ​ሴ​ንም መራራ ያደ​ረገ ሁሉን የሚ​ችል ሕያው አም​ላ​ክን!


ኢዮብ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ፍር​ዴን አስ​ወ​ገደ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ፥ ድንቅ ነገ​ርን የዱሮ እው​ነ​ተኛ ምክ​ርን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና አከ​ብ​ር​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል፥ አገ​ል​ጋዬ ነህና ይህን ዐስብ፤ እኔ ፈጥ​ሬ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ባሪ​ያዬ ነህ፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ር​ሳኝ።


ጽዮን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ኛል፤ ጌታም ረስ​ቶ​ኛል” አለች።


እኔ ግን፥ “በከ​ንቱ ደከ​ምሁ፤ ምንም ጥቅም ለሌ​ለ​ውና ለከ​ንቱ ጕል​በ​ቴን ፈጀሁ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ል​ኛል፤ መከ​ራ​ዬም በአ​ም​ላኬ ፊት ነው” አልሁ።


በጥ​ቂት ቍጣ ፊቴን ከአ​ንቺ ሰወ​ርሁ፤ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቸር​ነት ይቅር እል​ሻ​ለሁ፥ ይላል ታዳ​ጊሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告