Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 40:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወይስ ከማን ጋር ተመ​ካ​ከረ? ወይስ ማን መከ​ረው? ፍር​ድ​ንስ ማን አስ​ተ​ማ​ረው? የጥ​በ​ብ​ንስ መን​ገድ ማን አሳ​የው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍትህንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው? ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 40:14
9 交叉引用  

ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር።


ጥን​ቱን ዕው​ቀ​ት​ንና ምክ​ርን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? በነ​ፍሰ ገዳ​ዩስ የሚ​ፈ​ርድ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?


ሥራ​ው​ንስ የሚ​መ​ረ​ምር ማን ነው? ወይስ፦ ክፉ ሠር​ተ​ሃል የሚ​ለው ማን ነው?


ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበ​ርህ? ታስ​ተ​ውል እንደ ሆነ ንገ​ረኝ።


ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው የሚ​ና​ገር የለ​ምና፥ ከየ​ትም እንደ ሆኑ ብጠ​ይ​ቃ​ቸው አይ​መ​ል​ሱ​ል​ኝም።


የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


跟着我们:

广告


广告