Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 39:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን መጡ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “ወደ እኔ የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ?” አለው። ሕዝቅያስም፦ “ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ? አለው። ሕዝቅያስም፦ ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ አለው።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 39:3
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።


በዚ​ያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “በሶ​ርያ ንጉሥ ታም​ነ​ሃ​ልና፥ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​መ​ን​ህ​ምና ስለ​ዚህ የሶ​ርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእ​ጆ​ችህ አም​ል​ጠ​ዋል።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በን​ጉሡ በአ​ሜ​ስ​ያስ ላይ መጣ፤ እን​ዲ​ህም ሲል ነቢ​ይን ላከ​በት፥ “ሕዝ​ባ​ቸ​ውን ከአ​ንተ እጅ ያላ​ዳ​ኑ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ስለ​ምን ፈለ​ግ​ሃ​ቸው?”


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ለሞት እስ​ኪ​ደ​ርስ ታመመ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


“ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤


ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “በቤ​ትህ ያዩት ምን​ድን ነው?” አለው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤቴ፥ እን​ዲ​ሁም በቤተ መዛ​ግ​ብቴ ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው።


ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላ​ቶች ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ላይ ይጮ​ኻሉ ብላ​ችሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አውጁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝ​ብን ከሩቅ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋን​ቋ​ቸ​ው​ንም የማ​ታ​ው​ቀው፥ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም የማ​ታ​ስ​ተ​ው​ለው ሕዝብ ነው።


እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥


跟着我们:

广告


广告