Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 37:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 “ይህም ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ በዚህ ዓመት የዘ​ራ​ኸ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ቸሁ፤ ታጭ​ዱ​ማ​ላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ትተ​ክ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤ “በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ይህ ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዳላችሁ፤ ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፦ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የበቀለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ይህ ምልክት ይሆንሃል፥ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፥ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዱማላችሁ፥ ወይንንም ትተክላላችሁ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 37:30
12 交叉引用  

“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂ​ድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመ​ለስ?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ፈ​ጽ​መው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክቱ ይህ ይሆ​ን​ል​ሃል።


ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ማል፤ ወይ​ኑን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።


“ከጥ​ልቁ ወይም ከከ​ፍ​ታው ቢሆን ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምል​ክ​ትን ለአ​ንተ ለምን።”


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


ያ አም​ሳ​ኛው ዓመት ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም አት​ዝሩ፤ የገ​ቦ​ው​ንም አት​ጨዱ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም በእ​ርሱ አት​ል​ቀሙ።


跟着我们:

广告


广告