Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 37:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እነርሱም፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ብርታቱ የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱም ከሕዝቅያስ ተቀብለው ለኢሳይያስ የነገሩት መልእክት ይህ ነበር፦ “ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነርሱም፦ ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፥ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ኃይል የለም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 37:3
20 交叉引用  

እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ እና​ትም ለማ​ማጥ ኀይል የላ​ትም።


በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ል​ሰው ይፈ​ል​ጉ​ታል፤ እር​ሱም ይገ​ኝ​ላ​ቸ​ዋል።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥ በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤ መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።


ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሁ​ከ​ትና የጥ​ፋት፥ የመ​ረ​ገ​ጥና የስ​ብ​ራ​ትም ቀን በጽ​ዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖ​አል። ታና​ሹና ታላ​ቁም ሸሽ​ተው በተ​ራራ ላይ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛሉ።


ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


አቤቱ፥ ማረን፤ አን​ተን ተማ​ም​ነ​ና​ልና፤ የዐ​ላ​ው​ያን ዘራ​ቸው ለጥ​ፋት ነው፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን አንተ ነህ።


“ሳታ​ምጥ ወለ​ደች፤ ምጥም ሳያ​ገ​ኛት ወንድ ልጅን ወለ​ደች።


እኔ ተስ​ፋን ሰጠ​ሁሽ፤ አንቺ ግን አላ​ሰ​ብ​ሽ​ኝም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሴት እን​ድ​ት​ወ​ልድ፥ መካ​ንም እን​ዳ​ት​ሆን የማ​ደ​ርግ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?” ይላል አም​ላ​ክሽ።


ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል የለ​ምና፤ ያ የያ​ዕ​ቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ይድ​ናል።


ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告