Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 37:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አን​ተም በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ በኩል እን​ዲህ ብለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፦ በሰ​ረ​ገ​ላዬ ብዛት ወደ ተራ​ሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባ​ኖስ ራስ ወጥ​ቻ​ለሁ፤ ረዣ​ዥ​ሞ​ቹ​ንም ዝግ​ባ​ዎች፥ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም ጥዶች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ ወደ ከፍ​ታ​ውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገ​ባ​ለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በመልእክተኞችህ በኩል፣ በጌታ ላይ ብዙ የስድብ ቃል ተናገርህ፤ እንዲህም አልህ፤ ‘በሠረገሎቼ ብዛት፣ የተራሮችንም ከፍታ፣ የሊባኖስንም ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥም ዝግባዎችን፣ የተመረጡ ጥዶችን ቈርጫለሁ፤ እጅግ ወደራቁት ከፍታዎች፣ እጅግ ውብ ወደሆኑትም ደኖች ደርሻለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አንተም፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፥ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 37:24
21 交叉引用  

ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


ጠላ​ትም፦ ‘አሳ​ድጄ እይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ምር​ኮም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም አጠ​ግ​ባ​ታ​ለሁ፤ በሰ​ይ​ፌም እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በእ​ጄም እገ​ዛ​ለሁ’ አለ።


ያን​ጊዜ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች፥ ዛፎ​ችም ይጠ​ፋሉ። ነፍ​ስና ሥጋ​ንም ይበ​ላል፤ የሚ​ሸ​ሽም ከሚ​ነ​ድድ የእ​ሳት ነበ​ል​ባል እን​ደ​ሚ​ሸሽ ይሆ​ናል።


እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክቡ​ራ​ንን በኀ​ይል ያው​ካ​ቸ​ዋል፤ ታላ​ላ​ቆ​ች​ንም በሐ​ሣር ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ከፍ ያሉ​ትም ይዋ​ረ​ዳሉ።


ታላ​ላ​ቆ​ችም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሊባ​ኖ​ስም ከረ​ዣ​ዥም ዛፎች ጋር ይወ​ድ​ቃል።


የሊ​ባ​ኖስ ዛፎች፦ አንተ ከተ​ዋ​ረ​ድህ ጀምሮ ማንም ይቈ​ር​ጠን ዘንድ አል​ወ​ጣ​ብ​ንም ብለው በአ​ንተ ደስ አላ​ቸው።


ሊባ​ኖስ እንደ ፍሬ​ያማ እርሻ ሊለ​ወጥ፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈ​ጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይ​ይ​ደ​ለ​ምን?


ከታ​ና​ና​ሾቹ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን ጭፍራ ፊት መመ​ለስ እን​ዴት ትች​ላ​ለህ? ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች በግ​ብፅ የሚ​ታ​መኑ ለጌ​ታዬ ባሮች ናቸው።


ምና​ል​ባት በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ጌታው የአ​ሦር ንጉሥ የላ​ከ​ውን የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስን ቃል አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሰማው ቃል ይገ​ሥ​ጸው እንደ ሆነ፥ ስለ​ዚህ ለቀ​ረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


የሚ​አ​ጠ​ፋ​ህን ሰው በአ​ንተ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ዛፍ​ህ​ንም በም​ሳር ይቈ​ር​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላል።


ግብፅ እንደ ወንዝ ይነ​ሣል፤ ከባ​ሕ​ሩም እን​ደ​ሚ​ታ​ወክ ማዕ​በል ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዲህ ብሏል፥ “እነ​ሣ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ እከ​ድ​ና​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ንና የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ፊት​ህን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅና፤ ወደ መቅ​ደ​ሶ​ችም ተመ​ል​ከት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ላይ ትን​ቢት ተና​ገር።


跟着我们:

广告


广告