Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 36:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ የሠ​ራ​ዊቱ ጸሓፊ ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጡ፤ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ እንዲሁም ታሪክ መዝጋቢው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የጦር አዛዡ የተናገረውንም ሁሉ ነገሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊውም ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአስ፥ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ የቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የሕልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊው ሼብናና የታሪክ መዝጋቢ የነበረውም የአሳፍ ልጅ ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስም ቀርበው የአሦርያውያን ባለሥልጣን የተናገረውን ሁሉ አስረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 36:22
12 交叉引用  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ ገን​ዘብ ጠባ​ቂው ወደ ሳም​ናስ ሂድ እን​ዲ​ህም በለው፦


በዚ​ያም ቀን ባሪ​ያ​ዬን የኬ​ል​ቅ​ዩን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


እነሆ እና​ንተ ቀድሞ ትፈ​ሩ​አ​ቸው የነ​በሩ በግ​ር​ማ​ችሁ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የተ​ነሣ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ። መል​እ​ክ​ተ​ኞች መራራ ልቅ​ሶን እያ​ለ​ቀሱ ይላ​ካሉ፤ ሰላ​ም​ንም ይለ​ም​ናሉ።


ኤል​ያ​ቄ​ምና ሳም​ናስ፥ ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና እባ​ክህ፥ በሶ​ርያ ቋንቋ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ተና​ገር፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ አት​ና​ገ​ረን” አሉት።


የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።


ንጉ​ሡም፥ ይህ​ንም ቃል ሁሉ የሰሙ አገ​ል​ጋ​ዮቹ ሁሉ አል​ደ​ነ​ገ​ጡም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አል​ቀ​ደ​ዱም።


በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።


跟着我们:

广告


广告